የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድቤት ከሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድቤት እና ከድሬደዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድቤት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱ የተካሄደው አስተዳደራዊ ፍርድቤቱ ከሶማሌ ክልል፣ ከሀረሪ ክልል እና ከድሬደዋ አስተዳደር ለተወጣጡ የዳኝነትና የፍትህ አካላት ተሳታፊዎች የሁለተኛ ዙር ስልጠና በሚሰጥበት ወቅት ነው።
ሁለቱ ፍርድቤቶች በቀጣይ ከአስተዳደራዊ ፍርድቤቱ ጋር በመሆን ለዳኝነት እና ለፍትህ አካላት ስለ ካፒታል ገበያ በጋራ የስልጠና መድረኮችን ለማስተባበር እና ከካፒታል ገበያ ጋር የተያያዙ የፍርድቤት ክርክሮች ሲያጋጥሙ ተመሳሳይ የህግ ትርጉም እንዲኖር የሚያስችል ነው።

