ከሀረሪ እና ሶማሌ ክልል እንዲሁም ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ለተወጣጡ ተሳታፊዎች የስልጠና መድረክ ተዘጋጀ፡፡

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ከሀረሪ እና ሶማሌ ክልል እንዲሁም ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ለተወጣጡ ዳኞች፣ አቃቢያነ ህግ እና ሌሎች ተሳታፊዎች የሁለተኛ ዙር የስልጠና መድረክ አዘጋጅቷል።ስልጠናውን ላጠናቀቁ 70 ተሳታፊዎች ሰርተፊኬት ተሰጥቷል።
ስልጠናው በዋናነት የዳኞች እና የሕግ ባለሙያዎችን አቅም በማሣደግ በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለውን የካፒታል ገበያ ስርዓት ውጤታማ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡
አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ከሶማሌ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲሁም ከሶማሌ ክልል የፍትህ አካላት ባለሙያዎች ማሰልጠኛና የህግ ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን ስምምነቱ የስልጠናውን ተደራሽነት በማስፋት ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስራ ለመስራት የሚያግዝ ነው።

Newsletter Updates

Subscribe to receive the latest announcements, regulatory updates, and news from ECMAT

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት

በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን

መገኛችን

አራዳ ክፍለ ከተማ ፣ ፒያሳ ዋስትና ህንፃ 16ኛ ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ

+251111278823

admin@ecmat.gov.et

Follow Us

💬
ECMAT Digital Assistant
Welcome to the Ethiopian Capital Market Administrative Tribunal. How can I assist you with tribunal procedures or dispute resolution today?