የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድቤት ከሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክ/ከተማ አኔ ዲማ ወረዳ ለተወጣጡ አመራሮችና ወጣቶች capital market as an investment alternative for young innovators በሚል ርእስ የማነቃቂያ መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ የካፒታል ገበያ ምንነት፣ ለአገር ኢኮኖሚ እድገት ስለሚያበረክተው አስተዋጽኦ ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ ያለው ፋይዳ ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች ምቹ የሃብት ማሰባሰቢያ መንገድ ስለመሆኑ እንዲሁም ለኢንቨስተሮች ጥበቃ ያለው የህግና የአሰራር ማእቀፍ ተብራርቷል።
በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎች መድረኩ ጠቃሚ እንደነበር በመግለጽ፣ በቀጣይ የካፒታል ገበያን በጥልቀት የሚያስረዳ ተከታታይ እድል እንዲመቻች ፍላጎታቸውን አሳይተዋል።

