የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድቤት ከአማራ ክልል ለተወጣጡ የዳኝነት ና የፍትህ ተቋማት የሁለተኛ ዙር የስልጠና መድረክ አዘጋጅቷል።

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድቤት ከአማራ ክልል ለተወጣጡ የዳኝነት ና የፍትህ ተቋማት የሁለተኛ ዙር የስልጠና መድረክ አዘጋጅቷል።
በመድረኩ ከዚህ ቀደም ስልጠናውን ያገኙትን ከ60 በላይ ተሳታፊዎች በጥልቀት በማሰልጠን ሰርተፊኬት ተሰጥቷል።
ስልጠናው በዋናነት በሀገራችን የተጀመረው የካፒታል ገበያ ስርዓት ተዓማኒነት እንዲኖረው በተለይ የዳኝነት እና የፍትህ አካላት በካፒታል ገበያ ዙሪያ የሚነሱ ክርክሮችን ለመፍታት ተመሳሳይ የሆነ የህግ አተረጓጎም እንዲኖር ለማስቻል በህግ ማዕቀፉ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡
አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ በቀጣይ ከክልሉ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር ይህ ስልጠና በአማራ ክልል የፍትህ እና የህግ ኢንስቲቲዩት በኩል በቋሚነት የስልጠና ተቋሙ ውስጥ ለሚገቡ ሰልጣኞች እንዲሰጥ ለማድረግ የሚሰራ ሲሆን ይህም የስልጠናውን ተደራሽነት በማስፋት ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስራ ለመስራት ዝግጁ ነው።

Newsletter Updates

Subscribe to receive the latest announcements, regulatory updates, and news from ECMAT

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት

በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን

መገኛችን

አራዳ ክፍለ ከተማ ፣ ፒያሳ ዋስትና ህንፃ 16ኛ ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ

+251111278823

admin@ecmat.gov.et

Follow Us

💬
ECMAT Digital Assistant
Welcome to the Ethiopian Capital Market Administrative Tribunal. How can I assist you with tribunal procedures or dispute resolution today?