ፍርድ ቤት ከ2019 እስከ 2023 ዓ.ም የሚተገብረውን የአምስት ዓመት ረቂቅ ስትራቴጂክ እቅድ ከሰራተኞቹ ጋር ውይይት አካሄደ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ከ2019 እስከ 2023 ዓ.ም የሚተገብረውን የአምስት ዓመት ረቂቅ ስትራቴጂክ እቅድ ከሰራተኞቹ ጋር ውይይት አካሄደ።
ስትራቴጂክ እቅዱ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 ለፍርድ ቤቱ የተሰጡ ስልጣንና ኃላፊነቶችን መሰረት በማድረግ ከመንግስት ፖሊሲና አቅጣጫ ጋር በተጣጣመ መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ሶስት ዋና ዋና የትኩረት መስኮችን ያካትታል።
እነዚህም ተቋማዊ የመፈጸም፣ የማስፈጸምና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን ማሳደግ፣ ጥራት ያለውና ቀልጣፋ ውሳኔ በመስጠት የካፒታል ገበያውን ተዓማኒነት ማጠናከር እንዲሁም የካፒታል ገበያ የህግ ማዕቀፍ ስርጸት እና አጋርነትን ማጠናከር ናቸው።
በውይይቱ ከሰራተኞች በእቅዱ ውስጥ በተካተቱ ግቦች፣ ስትራቴጂዎችና ተግባራት ላይ ግብዓት የተገኘ ሲሆን በቀጣይ የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የውይይት መድረክ በማካሄድ ተጨማሪ ግብዓቶችን ለማካተት በዝግጅት ላይ ይገኛል።

Newsletter Updates

Subscribe to receive the latest announcements, regulatory updates, and news from ECMAT

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት

በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን

መገኛችን

አራዳ ክፍለ ከተማ ፣ ፒያሳ ዋስትና ህንፃ 16ኛ ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ

+251111278823

admin@ecmat.gov.et

Follow Us

💬
ECMAT Digital Assistant
Welcome to the Ethiopian Capital Market Administrative Tribunal. How can I assist you with tribunal procedures or dispute resolution today?