የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ::
ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በካፒታል ገበያ የህግ ምዕቀፎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በጋራ ለማዘጋጀት የሚያግዝ ሲሆን በተጨማሪም የካፒታል ገበያ የህግ ማዕቀፍ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት ተቋም ውስጥ የስርዓተ ትምህርቱ አካል እንዲሆን ለማድረግ ተነሳሽነቱን ወስደው በጋራ መስራት የሚያስችል ነው።
በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ለሀገራችን አዲስ በሆነው የካፒታል ገበያ የሕግ ማዕቀፍ እውቀትና ክህሎት ማሳደግ በዘርፉ ውስብስብ የሆኑ የፋይናንስ እና የኢንቨስትመንት የህግ ጉዳዮችን በመረዳት ፈጣንና ተገማች ውሳኔ እንዲሰጡ ለማስቻል ይህ ስምምነት ትልቅ ሚና ይጫወታል ።
ይህ ስምምነት በሁለቱ ተቋማት መካከል ዘላቂነት ያለው ትብብር በመፍጠር በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የካፒታል ገበያ የህግ አተረጓጎም ስርዓትን ለመፍጠር የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አጋርነት ነው።

