የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት እና የአፋር ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ::
ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት ስለ ካፒታል ገበያ የህግ ምዕቀፎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በጋራ ለማዘጋጀት የሚያግዝ ነው።
በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ለሀገራችን አዲስ በሆነው የካፒታል ገበያ የሕግ ማዕቀፍ እውቀትና ክህሎት በማሳደግ በዘርፉ ውስብስብ የሆኑ የፋይናንስ እና የኢንቨስትመንት የህግ ጉዳዮችን በመረዳት ፈጣንና ተገማች ፍትህ እንዲሰጡ ለማስቻል ይህ ስምምነት ትልቅ ሚና ይጫወታል ።
ይህ ስምምነት በሁለቱ ተቋማት መካከል ዘላቂነት ያለው ትብብር በመፍጠር በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የካፒታል ገበያ የህግ አተረጓጎም ስርዓትን ለመፍጠር የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አጋርነት ነው።
ስምምነቱ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዘመናዊውን የፋይናንስ ስርአት ለማስተናገድ ራሱን እያዘጋጀ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ለሌሎች ክልሎችም በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድ ነው::

