የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ከሸገር ከተማ አስተዳደር መነ አቢቹ ክፍለ ከተማ እና ከአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ጋር በትብብር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂዷል።
የ2018 ዓ.ም. የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ግብ ለማሳካት፣ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ከመነ አቢቹ ክፍለ ከተማ አመራሮች፣ ከአፍሪካ የልህቀት ማዕከል አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም ከክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ጋር በመሆን፣ “በጋራ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ከ9 ሺ በላይ ችግኞችን ተተክሏል።

