የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድቤት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድቤት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

አስተዳደራዊ ፍርድቤቱ በሩብ አመቱ ችሎቱን ዘመናዊና ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ በማደራጀት ማንኛውም የችሎት አገልግሎት ተጠቃሚ የችሎት ሂደቱን ባለበት ሆኖ መከታተል የሚያስችል ስርዓት አጠናቋል።

በተጨማሪም ከፌደራል እና ከኦሮሚያ ክልል ለተውጣጡ 97 የፍትህ ተቋማት ባለሞያዎችና ሃላፊዎች ስለ ካፒታል ገበያ ምንነት እና ተያያዥ ርዕሶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።
አስተዳደራዊ ፍርድቤቱ በአዲስ ዘመን እና ሪፖርተር ጋዜጣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፅሁፎች በሳምንት አንድ ጊዜ በማሳተም ህበረተሰቡ ስለ ካፒታል ገበያ እና ስለተቋሙ የስራ ሂደት መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል።

በ3 ወራት የቢሮ ኤርጎኖሚክስ ስራዎችም ተጠናቀዋል። በተጨማሪም በአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም የተቋሙን ሰራተኞች በማሳተፍ በሸገር ዙሪያ ሱሉልታ ክፍለ ከተማ መነ-አብቹ ወረዳ በሁለት ዙር 500 የአፕል፣ ዜቱናና እና ሌሎች አገር በቀል ችግኞችን መትከል ተችሏል።

ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው 25 ሰዎች ሁለት ሁለት የዕርባታ በጎች እና ለ50 ተማሪዎች የአንድ አመት የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል።

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድቤት በሩብ አመቱ ከተመደበለት በጀት 90 ነጥብ 4 በመቶ ስራ ላይ ማዋል ተችሏል።

እነዚህ በጠንካራ ጎን የታዩ በመሆኑ በቀጣይ የታየው ጥሩ አፈጻጸም ማስቀጠል ይገባል።

Newsletter Updates

Subscribe to receive the latest announcements, regulatory updates, and news from ECMAT

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት

በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን

መገኛችን

አራዳ ክፍለ ከተማ ፣ ፒያሳ ዋስትና ህንፃ 16ኛ ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ

+251111278823

admin@ecmat.gov.et

Follow Us

💬
ECMAT Digital Assistant
Welcome to the Ethiopian Capital Market Administrative Tribunal. How can I assist you with tribunal procedures or dispute resolution today?