የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በአማራ ክልል

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ከአማራ ክልል የፍትህ ተቋማት ለተወጣጡ ዳኞች፣ አቃቢያነ ህግ እና ከፍተኛ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እያካሄደ ነው።

አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ በባህርዳር ከተማ በመገኘት ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፍትህ ቢሮ፣ ከስነ ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ፣ከፖሊስ ኮሚሽን እና ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ለተወጣጡ ዳኞች፣ አቃቢያነ ህግ እና ከፍተኛ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ሰብሳቢ ዳኛ አቶ አብነት ዘርፉ: አስተዳደራዊ ፍርድቤቱ ከካፒታል ገበያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ብቻ በይግባኝ ለመመልከት የተቋቋመ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ዛሬ ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ስለ ካፒታል ገበያ ምንነት፣ የካፒታል ገበያ የህግ ማዕቀፎች እና የገበያው ተዋንያን ሃላፊነት እንዲሁም በገበያው ውስጥ የተከለከሉ ተግባራትን እና የሚያስከትሉትን ተጠያቂነት መረዳት ለግብይት ስርአቱ ስኬት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።

አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ በአማራ ክልል የሚገኙ የፍትህ ተቋማት ጋር በጋራ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

Newsletter Updates

Subscribe to receive the latest announcements, regulatory updates, and news from ECMAT

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት

በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን

መገኛችን

አራዳ ክፍለ ከተማ ፣ ፒያሳ ዋስትና ህንፃ 16ኛ ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ

+251111278823

admin@ecmat.gov.et

Follow Us

💬
ECMAT Digital Assistant
Welcome to the Ethiopian Capital Market Administrative Tribunal. How can I assist you with tribunal procedures or dispute resolution today?