የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በጋምቤላ ክልል

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ከጋምቤላ ክልል የፍትህ ተቋማት ለተወጣጡ ዳኞች፣ አቃቢያነ ህግ እና ከፍተኛ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እያካሄደ ነው።

አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ በጋምቤላ ከተማ በመገኘት ከጋምቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፍትህ ቢሮ፣ ከስነ ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ፣ከፖሊስ ኮሚሽን እና ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት፣ ንግድ ቢሮ፣ ፋይናንስ ቢሮ፣ ኢንቨስትመንት ቢሮ እንዲሁም ፕላን ቢሮ ለተወጣጡ ዳኞች፣ አቃቢያነ ህግ እና ከፍተኛ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ሰብሳቢ ዳኛ አቶ አብነት ዘርፉ:አስተዳደራዊ ፍርድቤቱ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከግብይቱ ጋር በተያያዘ በሚሰጣቸው ውሳኔዎች ላይ የሚቀርቡ ይግባኞችን መርምሮ የሚወስን ከመደበኛው ፍርድ ቤት የተለየ ነው ብለዋል።

የካፒታል ገበያ አዋጅ አንቀጽ 65 አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ በባለስልጣኑ ወይም የባለስልጣኑን ተግባርና ስልጣን በሚያስፈጽም ሰው በተላለፈ ውሳኔ ላይ የቀረበን ይግባኝ የመስማትና የመወሰን ስልጣን የተሰጠው መሆኑንም አቶ አብነት ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ዛሬ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ስለ ካፒታል ገበያ ምንነት፣ የካፒታል ገበያ የህግ ማዕቀፎች እና የገበያው ተዋንያን ሃላፊነት እንዲሁም በገበያው ውስጥ የተከለከሉ ተግባራትን እና የሚያስከትሉትን ተጠያቂነት መረዳት ለግብይት ስርአቱ ስኬት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።

በመድረኩ የክብር እንግዳ የነበሩት የጋምቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዘዳንት አቶ ጀምስ ዴንግ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የካፒታል ገበያ ጽንሰ ሀሳብ እንደ ሀገር አዲስ በመሆኑ እና ወደፊት ክልላችን ከአስተዳደራዊ ፍርድቤቱ ጋር ለሚያከናውናቸው ተግባር እንዲረዳ የእርስ በርስ ትውውቅ እና የልምድ ልውውጥ ማድረጉ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

አስተዳደራዊ ፍርድቤቱ ወደፊት ከተቋማችን ጋር ለሚያከናውነው ማንኛውም ተግባራት በጋራ ለመስራት ዝግጁ ነውም ብለዋል።

Newsletter Updates

Subscribe to receive the latest announcements, regulatory updates, and news from ECMAT

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት

በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን

መገኛችን

አራዳ ክፍለ ከተማ ፣ ፒያሳ ዋስትና ህንፃ 16ኛ ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ

+251111278823

admin@ecmat.gov.et

Follow Us

💬
ECMAT Digital Assistant
Welcome to the Ethiopian Capital Market Administrative Tribunal. How can I assist you with tribunal procedures or dispute resolution today?