የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ከሀረሪ ክልል እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ 17 የተለያዩ ተቋማት ለተወጣጡ 88 ተሳታፊዎች የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።
የሐረሪ ክልልና ድሬደዋ ከተማ እያደገ የመጣ የንግድ እንቅስቃሴ ያላቸው በመሆናቸው፣ ባለሀብቶች በካፒታል ገበያው ላይ ዘላቂ እምነት እንዲኖራቸው የአስተዳደራዊ ፍርድቤቱ ድርሻ ከማንኛውም ተቋም የሚበልጥ ነው።
የውይይት መድረኩ የተካሄደበት ወቅት ወቅቱን የጠበቀ እና በሀገራችን እያደገ ያለውን የኢንቨስትመንት ስርዓት በትክክል ለማስተናገድ ከማገዙም በላይ የእርስ በርስ ትውውቅ እና የልምድ ልውውጥ ማድረግ ወሳኝ ነው።
አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ በድሬደዋ ከተማ በመገኘት የተካሄደው የውይይት መድረክ ስለ ካፒታል ገበያ አዋጅ ያለውን ግንዛቤ አይን ገላጭ እንዲሆን በማሰብ የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣይም የካፒታል ገበያ የህግ ማእቀፍ፣ መመሪያዎችን እና አሰራር ስርዓቱን በተመለከተ የተለያዩ ሀገራት አለም አቀፍ ተሞክሮ እና በተግባር ልምምድ ማድረግን ያካተተ ሰፊ መድረክ ይዘጋጃል።
