የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድቤት የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን ጉብኝት

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድቤት በድሬደዋ ከተማ በመገኘት የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን ያከናወናቸውን ተግባራት ጉብኝት አድርጓል።

የድሬደዋ ፖሊስ ከዚህ ቀደም የነበረውን የከተማዋን ሰላም የሚያናጉ ተግባራትን ለመቀነስ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በማበልጽግ ሰላም የማስፈን ስራ እየሰራ እንደሆነም አስተዳደራዊ ፍርድቤቱ በድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያቤት በመገኘት የበለጸጉትን ቴክኖሎጂዎች ተመልክቷል።

የድሬደዋ ፖሊስ የሚከሰቱ ወንጀሎችን እና አደጋዎችን ለመቀነስ አገልግሎቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መንገድ በመደገፍ መስራቱን ተመልክተናል።

ኮሚሽኑ ከሚጠቀምበት ቴክኖሎጂዎች መካከል በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የበለጸገው “ኢኤፍፒ” መተግበሪያ ሲሆን ይህ መተግበሪያ ማንኛውም ዜጋ ስማርት ስልክ በመጠቀም ፎቶ ና ቪዲዮ በማንሳት ህገወጥ ተግባራትን ለፖሊስ የጥቆማ መረጃ የሚሰጥበት ነው።

በድሬደዋ ከተማ የሚገኙ ሆቴሎች፣ ገስት ሀውሶች እና ፔንሲዮኖች የሚገለገሉበት ሌላኛው የቴክኖሎጂ ስርዓት “ድሬ እንግዳ” የተሰኘው ዘመናዊ ሶፍትዌር ደግሞ ወደ ድሬደዋ የገባውን የማንኛውንም ሰው ሙሉ መረጃ የሚያሳውቅ እንደሆነ መመልከት ችለናል።

በተጨማሪም በድሬደዋ ከተማ አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎችና ባጃጆች የቀን ታክሲ እና የሌሊት ታክሲ በሚል የተለዩ በመሆናቸው ፖሊስ 24 የሚባለው የ24 ሰዓት ወንጀልና ሁነቶች አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር መሰረት ያለስምሪቱ የሚያሽከረክር ተሽከርካሪ ካለ በተላከው የጥቆማ ፎቶ መሰረት ሙሉ መረጃ መላክ እና አጠቃላይ ንጽጽር የሚሰጥ ከወረቀት አሰራር የጸዳ መሆኑን ።
ሌላኛው ቴክኖሎጂ “ታደግ” የሚባለው የትራፊክ አደጋ መረጃ ማስተዳደሪያ ስርዓት ሲሆን የትራፊክ ባለሙያውን ስምሪት በማሳለጥ በትራፊክ አደጋ የሚከሰቱ አደጋዎችን ቁጥር ለመቀነስ የሚያስችል እንደሆ የድሬደዋ ፖሊስ አመራሮች ገልጸዋል።

የአስተዳደራዊ ፍርድቤት ሰራተኞች የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያቤትን በጎበኙበት ሰዓት ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ የከተማው ነዋሪዎች የብሔራዊ መዝሙር ተዘምሮ ባንዲራ እስኪወርድ ድረስ ማንኛውንም እንቅስቃሴ በማቆም እንደሚጠብቁ ይህም ለሀገር ካላቸው ክብር ና ፍቅር መሆኑን ተመልክተናል።

Newsletter Updates

Subscribe to receive the latest announcements, regulatory updates, and news from ECMAT

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት

በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን

መገኛችን

አራዳ ክፍለ ከተማ ፣ ፒያሳ ዋስትና ህንፃ 16ኛ ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ

+251111278823

admin@ecmat.gov.et

Follow Us

💬
ECMAT Digital Assistant
Welcome to the Ethiopian Capital Market Administrative Tribunal. How can I assist you with tribunal procedures or dispute resolution today?