የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድቤት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፍትህና ፋይናንስ ሴክተር ተቋማት ለተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳኞች እና አቃቢያነ ህግ ጋር የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ ኢንቨስተሮች ጥበቃ ለማድረግ በክልሉ የሚገኙ ተቋማት ስለ ካፒታል ገበያ ምንነት፣ የካፒታል ገበያ የህግ ማዕቀፎች እና የአሰራር ስርዓትን በተመለከተ ግንዛቤን ማላቅ የውይይት መድረኩ አላማ ነው።
በተለይም ከካፒታል ገበያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ብቻ በይግባኝ የሚመለከት ልዩ ፍርድቤት ስራ መጀመሩን በማስተዋወቅ በጋራ ለሚሰሩ ስራዎች ዝግጁነት እንዲኖር የሚያስችል ነው። አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ በቀጣይ ለፍትህ ተቋማት ብቻ የሚሆን ጥልቀት ያለው ስልጠና በቅርቡ ይጀምራል።
