የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድቤት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዳኝነት፣ የፍትህና ፋይናንስ ሴክተር ተቋማት ለተወጣጡ ዳኞች፣ አቃቢያነ ህግ እና ከፍተኛ አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።
አስተዳደራዊ ፍርድቤቱ የውይይት መድረክ ያዘጋጀበት ዋና አላማ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ተቋማት ጋር ወደፊት ለሚያከናውናቸው ስራዎች የትውውቅ እና የዘርፉን ምንነት በተመለከተ ግንዛቤ የሚፈጥር ነው።
በተለይም የአስተዳዳራዊ ፍርድቤቱ መቋቋም የገበያ ታማኝነትን የሚያጠናክር፣የኢንቨስተሮችን አመኔታ የሚያጎለብት እና የካፒታል ገበያ አለመግባባቶችን ለመፍታት ፍትሃዊ፣ግልጽ እና ቀልጣፋ አሰራርን የሚከተል ነው።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ወይም የባለስልጣኑን ተግባርና ስልጣን በሚያስፈጽም ሰው በተላለፉ ውሳኔዎች ላይ የሚቀርቡ ይግባኞችን መርምሮ የሚወስን ከመደበኛው ፍርድቤት የተለየ ተቋም መሆኑን ተሳተፊዎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል።
