የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ዋነኛ ተግባሩ በካፒታል ገበያ ባለስልጣን ወይም የባለስልጣኑን ተግባርና ኃላፊነት በሚያስፈጽም ሰው በተሰጠ ውሳኔላይ የሚቀርብ የይግባኝ አቤቱታን መርምሮ መዳኘት በመሆኑ ማንኛውም ቅሬታ ያለው ሰው ወደ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ቀርቦ ይግባኝ መጠየቅ ይችላል::

የይግባኝ መብት አጠቃቀም

ይግባኝ የሚጠየቅባቸው ጉዳዮች?
  • የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ መከልከል፣ የአገልግሎት ሰጭነት ፈቃድ መታገድ እና መሰረዝ
  • ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ለማስመዝገብ ወይም ለመሸጥ የተደረገ ክልከላ
  • አስተዳደራዊ እርምጃዎች እና የገንዘብ ቅጣቶች
ይግባኝ ማለት የሚችለው ማን ነው?

በካፒታል ገበያ ባለሰልጣን ወይም የባለስልጣኑን ተግባር በሚያስፈጽም ሰው በተሰጠ ውሳኔ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ማለትም፡

  • የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ደላሎች፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ አከናዋኞች፣የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ዲጂታል ንዑስ-ደላላዎች፣ኢንቨስትመንት ባንኮች፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪዎች፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ሸሪኣ አማካሪዎች፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ሮቦ አማካሪዎች፣ የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ ስራ አከናዋኝ ፣ክራውድ ፈንዲንግ አገናኞች፣የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ከፋቾች፣የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ጠባቂዎች፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ፖርትፎሊዮ ስራ አስኪያጆች፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገማች ድርጅቶችና ተሿሚ እንደራሴዎች ውሳኔው በደረሳቸው 28 የስራ ቀናት ውሰድጥ ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የይግባኝ አቀራረብ ስርዓት
  1. ይግባኝ ለማቅረብ የሚያስችል በካፒታል ገበያ ባለስልጣን ወይም የባለስልጣኑ ስልጣንና ተግባር በሚያስፈጽም ሰው የተሰጠ ውሳኔ መያዝ
  2. የይግባኝ አቤቱታን ከማስረጃዎች ጋር ማዘጋጀት
  3. ያዘጋጁትን የይግባኝ አቤቱታ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በይነ- መረብ ወይም በአካል አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ተገኝቶ ማቅረብ
  4. በክፍያ ሰንጠረዥ ላይ በተቀመጠው መሰረት የይግባኝ ፋይል መክፈቻ አገልግሎት ክፍያ መክፈል
  5. ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃ በበይነ-መረብ መከታተል

የተቀናጀ የጉዳይ አያያዝ

ይግባኝ ለማቅረብ ወይም በሂደት ላይ ያለ ጉዳይን ለመከታል ደህንነቱ የተጠበቀውን ይህንን መግቢያ ይጠቀሙ

የአገልግሎት መስኮች

የቨርቹዋል የፍርድ ቤት አገልግሎት

የቨርቹዋል ፍርድ ቤት አገልግሎት ተከራካሪ ወገኖች በአካል መገኘት ሳያስፈልጋቻው በዙም መተግበሪያ ባሉበት ሆነው ችሎቱን የሚከታተሉበት ስርዓት ነው፡፡

የሬጅስትራር አገልግሎት

የይግባኝ አቤቱታዎች የጊዜ ገደብና የስነ-ስርዓት ሕግን ማሟላታቸውን ማረጋገጥ፣ ክፍያ አስከፍሎ ፋይል መክፈት፣ የችሎት ትዕዛዞችን በፍጥነት ለሚመለከታቸው ወገኖች ማድረስ፣ የሰነድ ግልባጭ እና ሌሎች አገልግሎቶች ይሰጡበታል፡፡

እለታዊ ቀጠሮ

የፍርድ ቤቱ የየእለት ቀጠሮዎች በዚህ ይለጠፋሉ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት

በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን

መገኛችን

አራዳ ክፍለ ከተማ ፣ ፒያሳ ዋስትና ህንፃ 16ኛ ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ

+251111278823

admin@ecmat.gov.et

Follow Us

💬
ECMAT Digital Assistant
Welcome to the Ethiopian Capital Market Administrative Tribunal. How can I assist you with tribunal procedures or dispute resolution today?