የሬጅስትራር አገልግሎት ሬጅስትራሩ ተጠሪነቱ ለሰብሳቢ ዳኛ ሲሆን፣ በቨርቹዋል ወይም በአካል የቀረቡ ሁሉንም የይግባኝ አቤቱታዎች ጊዜ ያላለፈባቸውና በስነ ስርዓት ህጉ መሰረት መሟላታቸውን መርምሮ የማረጋገጥ ግዴታና ኃላፊነት አለበት። በተጨማሪም መጥሪያዎች ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሱ ማድረግ፣ ለይግባኝ አቤቱታዎች መመዝገቢያ መዝገብ መያዝ፣ የችሎት ሂደቶችን ቅጂዎች መያዝና መጠበቅ፣ ለአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ሰነዶችን መቀበል፣ ከሬጅስትራር ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ደብዳቤዎችን መቀበልና መከታተል፣ እንዲሁም በአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ አባላት፣ በክርክር ሂደቱ ውስጥ ተሳታፊ ለሆኑ አካላት እና አግባብነት ባላቸው ባለስልጣናት መካከል ዋነኛ የመገናኛ መስመር በመሆን ውጤታማ ቅንጅት እንዲኖር ማረጋገጥ ይጠበቅበታል። ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮች ግልባጭ ለመጠየቅ ሬጅስትራር አገልግሎትየጠያቂው መረጃሙሉ ስምየፋይዳ መታወቂያ ቁጥርኢ. ሜይልየሰነድ ግልባጭ የተጠየቀበት ምክንያትአስገባ
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን ፈጣን አገናኞች መነሻ ገፅአገልግሎቶችስለ እኛዜናዎች ግብዓቶች ተደጋጋሚ ጥያቄዎችአርቲክል እና ጆርናሎችአዋጆችደንቦችመመሪያዎች መገኛችን አራዳ ክፍለ ከተማ ፣ ፒያሳ ዋስትና ህንፃ 16ኛ ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ +251111278823 admin@ecmat.gov.et Follow Us