በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችዎ
እባክዎ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ምን እንደሆነ ያስረዱኝ?
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 (አንቀጽ 64) መሠረት የተቋቋመ ልዩ እና ገለልተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ወይም የባለስልጣኑን ተግባርና ኃላፊነት በሚያስፈጽም ሰው የተላለፉ ውሳኔዎች ላይ የሚነሱ ይግባኞችን በፍትሐዊነት፣ በፍጥነትና በሙያዊ ብቃት ይመርመራል።
መደበኛ ፍርድ ቤቶች እያሉ ልዩ የሆነ አስተዳራዊ ፍርድ ቤት መመስረት ለምን አስፈለገ ?
አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ የተቋቋመው ከካፒታል ገበያ ጋር የተያያዙ ክርክሮችን በፍጥነትና በብቃት ተገማች ውሳኔ ለመስጠት እንዲቻል ሲሆን እነዚህ ክርክሮች በቶሎ ውሳኔ ካላገኙ ገበያው ላይ የሚኖርን እምነት የሚሸረሽር በመሆኑ መደበኛ ፍርድ ቤቶች ደግሞ ከሚከተሉት ጥብቅ የስነ ስርዓት ሂደትና ካለባቸው የፋይል ብዛት አኳያ አመቺ ባለመሆናቸው ምክንያት ነው፡፡
አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ውሳኔዎቹን የማስፈፀም ስልጣን አለው?
አዎን። ፍርድ ቤቱ በፍትሐ ብሔር ሥነ–ሥርዓት ህግ መሠረት መደበኛ ፍርድ ቤቶች ያላቸውን የማስፈጸሚያ ሥልጣን አለው። ምስክሮችን ሊጠራ፣ ሰነዶች እንዲቀርቡ ሊያዝ፣ ትእዛዞችን ሊሰጥ እና ውሳኔዎቹን ለማስፈፀም የፖሊስ ድጋፍ ሊጠይቅ ይችላል።