ስለ የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 1284/2013 አንቀፅ 64 መሰረት የተቋቋመ ልዩ የፍትህ ተቋም ነው፡፡

የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ወይም የባለስልጣኑ ተግባርና ኃላፊነት ያለው ሰውበሰጠው ውሳኔ ላይ በይግባኝ የሚቀርቡለትን አቤቱታዎች ተቀብሎ የሚዳኝ ሲሆን ተግባሩን በፍትሃዊነት ፣በግልጽነትና በታማኝነት ነፃና ገለልተኛ በሆነ ሁኔታ ያከናውናል፡፡

የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስቴር የሚሾሙ ሰብሳቢ ዳኛ፣ ም/ሰብሳቢ እና ሌሎች ሶስት ዳኞች የሚኖሩት የሚሰሩት ሲሆን ዳኞቹ በሰነድ ሙዓለ ንዋይ፣ በፋይናንስ ሂሳብ አያያዝ ልዩ ሙያዊ አያያዝ ያላቸው ናቸው፡፡

ርዕይ

በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን

ዓላማ

ለተከራካሪ ወገኖች ተአማኒና ቀልጣፋ ውሳኔዎችን በመስጠት የሰነደ ሙዓለ-ንዋይ ግብይት ስርዓቱን ጤናማነት እና ክብር ማስጠበቅ

  • በገለልተኝነት እና በፍትሃዊነት ውሳኔዎች የመስጠት
  • የሙያ ብቃቱ የተረጋገጠ የግብይት ስርዓቱን ጤናማነት የሚያስጠብቅ ውሳኔ የሚሰጥ ተቋም መሆን
  • የግብይት ስርዓቱ ከተከለከሉ የግብይት ተግባራት የፀዱ እንዲሆን ማስቻል
  • የኢንቨስተሮች መብትና ጥቅም የተረጋገጠበት የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ግብይት መኖሩን ማረጋገጥ 

ተልዕኳችን

በሰነደ-ሙዓለ ንዋይ ግብይት ዙሪያ ለሚከሰቱ እና ለሚያጋጥሙ ክርክሮች እና አለመግባባቶች ቀልጣፋ፣ ተዓማኒ፣ ፍትሀዊ እና ግልጽ የሆነ ተገማች ውሳኔ መስጠት

እሴት

  • ገለልተኝነት
  • ግልጸኝነት
  • ቀልጣፋነት
  • ተደራሽነት
  • ተጠያቂነት
  • ሚስጥር ጠባቂት
  • የሙያ ብቃት

የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ አባላት

የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ አባላት በሕግና በካፒታል ገበያ ዘርፍ ለረጅም አመታት የካበተ ልምድ አላቸው

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት

በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን

መገኛችን

አራዳ ክፍለ ከተማ ፣ ፒያሳ ዋስትና ህንፃ 16ኛ ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ

+251111278823

admin@ecmat.gov.et

Follow Us

💬
ECMAT Digital Assistant
Welcome to the Ethiopian Capital Market Administrative Tribunal. How can I assist you with tribunal procedures or dispute resolution today?