የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ከ FSD Ethiopia ጋር በመተባበር ለዳኞች እና የህግ ባለሞያዎች የሚያገለግል “Capital Market Guide Book for Judges and Lawyers” የተሰኘ መጸሀፍ የመጀመሪያ ረቂቅ አጠናቋል።
279 ገፆች ያሉት ይህ ረቂቅ መፅሀፍ ስለ ካፒታል ገበያ አጠቃላይ ፅንሰ ሃሳቦች እንዲሁም የካፒታል ገበያ ተሳታፊዎች፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ከፋች (Market Maker)፣ የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ ሥራ አከናዋኞች (Collective Investment Scheme Operators) እና ሌሎችም አገልግሎት ሰጪዎች በገበያው የሚያከናውኗቸው ተግባራት ምን እንደሆኑ በዝርዝር ይዟል።
በተጨማሪም ኢንቬስተር ማነው፣ ለኢንቨስተሮች የተደረገ ጥበቃ፤ በግብይት ስርዓት ውስጥ የተከለከሉ ተግባራት ምንድናቸው፣ በገበያው የሚሳተፉ ተዋንያን የተከለከሉ ተግባራትን ቢፈጽሙ የሚያስከትሉትን የቅጣት አይነቶች፣ የተከለከሉ ተግባራትን መፈጸም በኢኮኖሚው ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ከውጭ ሀገራት የተገኙ ተሞክሮዎችን ጭምር ያካተተ ረቂቅ ነው።
በካፒታል ገበያ ስነምህዳር ያሉ አማራጭ የግጭት አፈታት ስርአቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ተግባርና ሃላፊነት፤ በግብይት ስርአቱ ውስጥ የሚጠበቅበት ሚና ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ጋር ያለው ትስስር በጋይድ ቡኩ ከተመላከቱ አበይት ጉዳዮች ጥቂቶች ናቸው።
ሰነዱ ለአገራችን የህግ ባለሞያዎች እንዲሁም ስለካፒታል ገበያ ማወቅ ለሚፈልጉ ሁሉ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ በረቂቅ መጸሀፉ ላይ ያለዎትን አስተያየት ከታች ተቀመጠው ኢሜይል እንዲያጋሩን ከአክብሮት ጋር ተጋብዘዋል።
Email : SELAMAWIT.MENGESHA@ecmat.gov.et