በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን

ገለልተኝነት
ግልጸኝነት
ቀልጣፋነት
ተደራሽነት
ተጠያቂነት
ሚስጥር ጠባቂነት
የሙያ ብቃት

ተግባራችን

የካፒታል ገበያንአስተማማኝ እና ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን የሚነሱ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያስችል ገለልተኛ ተቋም አስፈላጊ ነው፡፡ የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ የኢንቨስተሮችን ጥበቃ በማረጋገጥና የካፒታል ገበያ ተዓማኒነት እንዲኖረው በማስቻል የተረጋጋ የካፒታል ገበያን ለመፍጠር ይሰራል፡፡

አስተዳደራዊ ውሳኔን በይግባኝ መዳኘት

በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ወይም የባለስልጣኑን ስልጣንና ተግባር በሚያፈጽም ሰው በተሰጠ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ለአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ የሚያቀረበውን ይግባኝ መርምሮ ውሳኔ መስጠት

ገለልተኛ የፍርድ ሂደት

የቀረቡ የይግባኝ አቤቱታዎችን ሙያዊ ስነምግባርን በተላበሰ ገለልተኝነት ይዳኛል

ተደራሽነት እና ግልጽነት

የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ለሁሉም ተከራካሪ ወገኖች ተደራሽ ና ችሎቱን ግልጽ በማድረግ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ

ግንዛቤ መፍጠር

ለባለድርሻ አካላት ስልጠና በመስጠት እንዲሁም በጋዜጣ፣ በመጽሄት፣በጆርናል እና በተለያዩ ሚዲያዎች ስለ ካፒታል ገበያ ምንነት እና ስለ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ስልጣንና ተግባር ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ይሰራል፡፡

የተቀናጀ የጉዳይ አያያዝ

ይግባኝ ለማቅረብ ወይም በሂደት ላይ ያለ ጉዳይን ለመከታል ደህንነቱ የተጠበቀውን ይህንን መግቢያ ይጠቀሙ

የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ መሰረቶች

ልዩ ሙያዊ እውቀትና ክህሎት

የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ አባላት በሰነደ ሙዓለ ንዋይ፣በንግድ ፣በፋይናንስ ሂሳብ አያያዝ ልዩ ሙያዊ እውቀት እና ክህሎት ያላቸው መሆኑ

የዳኝነት ነፃነት

በአዋጅ ቁጥር 1248/2013 መሰረት በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ወይም የባለስልጣኑን ስልጣንና ተግባር በሚያስፈጽም ሰው በተላለፈ ውሳኔ ላይ የሚቀርብን የይግባኝ አቤቱታ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ እንዲዳኝ ራሱን ችሎ የተቋቋመ መሆኑ

ግልጽነት

ግልጽነትና ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ለህዝብ ክፍት የሆነ ችሎት መኖሩ

ቀልጣፋና ጥራቱ የተጠበቀ ሂደት

ለአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ የሚቀርቡጉዳዮች የሚዳኙበት ሂደት ጥራቱን የጠበቀና ቀልጣፋ መሆኑ

የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ አባላት

የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ አባላት በሕግና በካፒታል ገበያ ዘርፍ ለረጅም አመታት የካበተ ልምድ አላቸው

የተከበሩ አቶ አብነት ዘርፉ አብርሃም

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ሰብሳቢ ዳኛ

ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ሽፈራው ኃይለገብርኤል

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር

የቅርብ ጊዜ ውሳኔዎችና ዜናዎች

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት

በካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር አፍሪካዊ የፍትህ ተምሳሌት መሆን

መገኛችን

አራዳ ክፍለ ከተማ ፣ ፒያሳ ዋስትና ህንፃ 16ኛ ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ

+251111278823

admin@ecmat.gov.et

Follow Us

💬
ECMAT Digital Assistant
Welcome to the Ethiopian Capital Market Administrative Tribunal. How can I assist you with tribunal procedures or dispute resolution today?